መጽሐፈ ነህምያ።

1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13


ምዕራፍ 11

የሕዝቡም አለቆች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፤ ከቀሩትም ሕዝብ ከአሥሩ ክፍል አንዱ በቅድስቲቱ ከተማ በኢየሩሳሌም፥ ዘጠኙም በሌሎች ከተሞች ይቀመጡ ዘንድ ዕጣ ተጣጣሉ።
2 ፤ ሕዝቡም በፈቃዳቸው በኢየሩሳሌም ለመቀመጥ የወደዱትን ሰዎች ሁሉ ባረኩ።
3 ፤ በኢየሩሳሌምም የተቀመጡት የአገሩ አለቆች እነዚህ ናቸው፤ እስራኤል ግን ካህናቱም ሌዋውያኑም ናታኒምም የሰሎሞንም ባሪያዎች ልጆች እያንዳንዳቸው በየርስታቸውና በየከተማቸው በይሁዳ ከተሞች ተቀመጡ።
4 ፤ ከይሁዳና ከብንያምም ልጆች እነዚህ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ። ከይሁዳ ልጆች፤ ከፋሬስ ልጆች የመላልኤል ልጅ የሰፋጥያስ ልጅ የአማርያ ልጅ የዘካርያስ ልጅ የዖዝያ ልጅ አታያ፤
5 ፤ የሴሎናዊውም ልጅ የዘካርያስ ልጅ የዮያሪብ ልጅ የዓዳያ ልጅ የዖዛያ ልጅ የኮልሖዜ ልጅ የባሮክ ልጅ መዕሤያ።
6 ፤ በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የፋሬስ ልጆች ሁሉ አራት መቶ ስድሳ ስምንት ጽኑዓን ነበሩ።
7 ፤ የብንያምም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ የየሻያ ልጅ የኢቲኤል ልጅ የመዕሤያ ልጅ የቆላያ ልጅ የፈዳያ ልጅ የዮእድ ልጅ የሜሱላም ልጅ ሰሉ።
8 ፤ ከእርሱም በኋላ ጌቤና ሳላይ ዘጠኝ መቶም ሀያ ስምንት።
9 ፤ አለቃቸውም የዝክሪ ልጅ ኢዮኤል ነበረ፤ የሐስኑአም ልጅ ይሁዳ በከተማው ላይ ሁለተኛ ነበረ።
10 ፤ ከካህናቱ፤ የዮያሪብ ልጅ ዮዳኤ፥ ያኪን፥
11 ፤ የእግዚአብሔርም ቤት አለቃ የአኪጦብ ልጅ የመራዮት ልጅ የሳዶቅ ልጅ የሜሱላም ልጅ የኪልቅያስ ልጅ ሠራያ፥
12 ፤ የቤቱንም ሥራ የሠሩ ወንድሞቻቸው ስምንት መቶ ሀያ ሁለት፤ የመልክያ ልጅ የፋስኮር ልጅ የዘካርያስ ልጅ የአማሲ ልጅ የፈላልያ ልጅ የይሮሐም ልጅ ዓዳያ፥
13 ፤ ወንድሞቹም የአባቶቹ ቤቶች አለቆች ሁለት መቶ አርባ ሁለት፤ የኢሜር ልጅ የምሺሌሞት ልጅ የአሕዛይ ልጅ የኤዝርኤል ልጅ አማስያ፥
14 ፤ ወንድሞቻቸውም መቶ ሀያ ስምንት ጽኑዓን ኃያላን፤ አለቃቸውም የሐግዶሊም ልጅ ዘብድኤል ነበረ።
15 ፤ ከሌዋውያንም፤ የቡኒ ልጅ የአሳብያ ልጅ የዓዝሪቃም ልጅ የአሱብ ልጅ ሻማያ፤
16 ፤ ከእግዚአብሔርም ቤት በሜዳ በነበረው ሥራ ላይ የነበሩ የሌዋውያን አለቆች ሳባታይና ዮዛባት፤
17 ፤ በጸሎትም ጊዜ ምስጋናን የሚቀነቅኑ አለቃው የአሳፍ ልጅ የዘብዲ ልጅ የሚካ ልጅ መታንያ፥ በወንድሞቹም መካከል ሁለተኛ የነበረ በቅበቃር፥ የኤዶታምም ልጅ የጋላል ልጅ የሳሙስ ልጅ አብድያ።
18 ፤ በቅድስቲቱ ከተማ የነበሩ ሌዋውያን ሁሉ ሁለት መቶ ሰማንያ አራት ነበሩ።
19 ፤ በሮቹንም የሚጠብቁ በረኞቹ፥ ዓቁብና ጤልሞን ወንድሞቻቸውም፥ መቶ ሰባ ሁለት ነበሩ።
20 ፤ ከእስራኤልም የቀሩት ከካህናትና ከሌዋውያንም እያንዳንዳቸው በየርስታቸው በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ውስጥ ነበሩ።
21 ፤ ናታኒምም በዖፌል ተቀምጠው ነበር፤ ሲሐና ጊሽጳ በናታኒም ላይ ነበሩ።
22 ፤ በእግዚአብሔርም ቤት ሥራ ላይ ከነበሩ መዘምራን ከአሳፍ ልጆች ወገን የሚካ ልጅ የመታንያ ልጅ የሐሸብያ ልጅ የባኒ ልጅ ኦዚ በኢየሩሳሌም የሌዋውያን አለቃ ነበረ።
23 ፤ ስለ እነርሱም የንጉሥ ትእዛዝ ነበረ፤ የመዘምራኑም ሥርዓት ለየዕለቱ የተሠራ ነበረ።
24 ፤ ከይሁዳም ልጅ ከዛራ ወገን የሜሴዜቤል ልጅ ፈታያ ስለ ሕዝቡ ነገር ሁሉ በንጉሡ አጠገብ ነበረ።
25 ፤ ስለ መንደሮቹና ስለ እርሾቻቸው፤ ከይሁዳ ልጆች አያሌዎች በቂርያትአርባቅና በመንደሮችዋ፥ በዲቦንና በመንደሮችዋም፥ በይቀብጽኤልና በመንደሮችዋም፥
26
27 ፤ በኢያሱ፥ በሞላዳ፥ በቤትጳሌጥ፥ በሐጸርሹዓል፥
28 ፤ በቤርሳቤህና በመንደሮችዋ፥ በጺቅላግ፥
29 ፤ በምኮናና በመንደሮችዋ፥ በዓይንሪሞን፥
30 ፤ በጾርዓ፥ በየርሙት፥ በዛኖዋ በዓዶላም በመንደሮቻቸውም፥ በለኪሶና በእርሻዎችዋ፥ በዓዜቃና በመንደሮችዋ ተቀመጡ። እንዲሁ ከቤርሳቤህ ጀምሮ እስከ ሄኖም ሸለቆ ድረስ ሰፈሩ።
31 ፤ የብንያምም ልጆች ከጌባ ጀምሮ በማክማስ፥ በጋያ፥
32 ፤ በቤቴልና በመንደሮችዋ፥ በዓናቶት፥ በኖብ፥
33
34 ፤ በሐናንያ፥ በሐጾር፥ በራማ፥ በጊቴም፥ በሐዲድ፥
35 ፤ በስቦይም፥ በንበላት፥ በሎድ፥ በኦኖ፥ በጌሐራሺም ተቀመጡ።
36 ፤ በይሁዳም ከነበሩ ሌዋውያን አያሌ ክፍሎች ወደ ብንያም ሆኑ።