መጽሐፈ ነህምያ።

1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13


ምዕራፍ 12

ከሰላትያል ልጅ ከዘሩባቤልና ከኢያሱ ጋር የወጡት ካህናትና ሌዋውያን እነዚህ ነበሩ፤
2 ፤ ሠራያ፥ ኤርምያስ፥ ዕዝራ፥ አማርያ፥
3 ፤ መሉክ፥ ሐጡስ፥ ሴኬንያ፥ ሬሁም፥ ሜሪሞት፥
4
5 ፤ አዶ፥ ጌንቶን፥ አብያ፥ ሚያሚን
6 ፤ መዓድያ፥ ቢልጋ፥ ሸማያ፥ ዮያሪብ፥ ዮዳኤ፥
7 ፤ ሰሉ፥ ዓሞቅ፥ ኬልቅያስ፥ ዮዳኤ፤ እነዚህ በኢያሱ ዘመን የካህናቱና የወንድሞቻቸው አለቆች ነበሩ።
8 ፤ ሌዋውያኑም፤ ኢያሱ፥ ቢንዊ፥ ቀድምኤል፥ ሰራብያ፥ ይሁዳ፥ ከወንድሞቹም ጋር በመዘምራን ላይ የነበረ መታንያ።
9 ፤ ወንድሞቻቸውም በቅቡቅያና ዑኒ በየሰሞናቸው በአንጻራቸው ነበሩ።
10 ፤ ኢያሱም ዮአቂምን ወለደ፥ ዮአቂምም ኤልያሴብን ወለደ፥ ኤልያሴብም ዮአዳን ወለደ፥
11 ፤ ዮአዳም ዮናታንን ወለደ፥ ዮናታንም ያዱአን ወለደ።
12 ፤ በዮአቂምም ዘመን የአባቶች ቤቶች አለቆች እነዚህ ካህናቱ ነበሩ፤ ከሠራያ ምራያ፥
13 ፤ ከኤርምያስ ሐናንያ፥ ከዕዝራ ሜሱላም፥
14 ፤ ከአማርያ ይሆሐናን፥ ከመሉኪ ዮናታን፥
15 ፤ ከሰበንያ ዮሴፍ፥ ከካሪም ዓድና፥ ከመራዮት ሔልቃይ፥
16 ፤ ከአዶ ዘካርያስ፥ ከጌንቶን ሜሱላም፥
17 ፤ ከአብያ ዚክሪ፥ ከሚያሚን ሞዓድያ፥
18 ፤ ፈልጣይ፥ ከቢልጋ ሳሙስ፥ ከሸማያ ዮናታን፥
19 ፤ ከዮያሪብ መትናይ፥ ከዮዳኤ ኦዚ፥
20 ፤ ከሳላይ ቃላይ፥ ከዓሞቅ ዔቤር፥
21 ፤ ከኬልቅያስ ሐሸብያ፥ ከዮዳኤ ናትናኤል።
22 ፤ ከሌዋውያኑም በኤልያሴብና በዮአዳ፥ በዮሐናንና በያዱአ ዘመን የአባቶች ቤቶች አለቆች ተጻፉ፤ ካህናቱም በፋርሳዊው በዳርዮስ መንግሥት ዘመን ተጻፉ።
23 ፤ የሌዊ ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆች እስከ ኤልያሴብ ልጅ እስከ ዮሐናን ዘመን ድረስ በታሪክ መጽሐፍ ተጻፉ።
24 ፤ የሌዋውያኑም አለቆች፤ ሐሸብያ፥ ሰራብያ፥ የቀድምኤልም ልጅ ኢያሱ እንደ እግዚአብሔር ሰው እንደ ዳዊት ትእዛዝ በየሰሞናቸው በወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ያከብሩና ያመሰግኑ ነበር።
25 ፤ መታንያ፥ በቅቡቅያ፥ አብድዮ፥ ሜሱላም፥ ጤልሞን፥ ዓቁብ በበሮች አጠገብ የሚገኙትን ዕቃ ቤቶች ለመጠበቅ በረኞች ነበሩ።
26 ፤ እነዚህ በኢዮሴዴቅ ልጅ በኢያሱ ልጅ በዮአቂም በአለቃውም በነህምያ በጸሐፊውም በካህኑ በዕዝራ ዘመን ነበሩ።
27 ፤ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር በቀደሱ ጊዜ ቅዳሴውን በደስታና በምስጋና በመዝሙርም በጸናጽልም በበገናም በመሰንቆም ለማድረግ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጡአቸው ዘንድ ሌዋውያኑን በየስፍራቸው ሁሉ ፈለጉ።
28
29 ፤ መዘምራኑም በኢየሩሳሌም ዙሪያ መንደሮች ሠርተው ነበርና የመዘምራኑ ልጆች ከኢየሩሳሌም ዙሪያና ከነጦፋውያን መንደሮች፥ ከቤትጌልገላም፥ ከጌባና ከዓዝሞት እርሻዎች ተሰበሰቡ።
30 ፤ ካህናቱና ሌዋውያኑም ራሳቸውን አነጹ፤ ሕዝቡንም በሮቹንም ቅጥሩንም አነጹ።
31 ፤ የይሁዳንም አለቆች ወደ ቅጥሩ ላይ አወጣኋቸው፤ አመስጋኞቹንም በሁለት ታላላቅ ተርታ አቆምኋቸው፤ አንዱም ወደ ቀኝ በቅጥሩ ላይ ወደ ጕድፍ መጣያው በር ሄደ።
32 ፤ ከእነርሱም በኋላ ሆሻያ፥ የይሁዳም አለቆች እኵሌታ፥
33 ፤ ዓዛርያስ፥ ዕዝራ፥
34 ፤ ሜሱላም፥ ይሁዳ፥ ብንያም፥ ሸማያ፥ ኤርምያስ፥
35 ፤ መለከትም ይዘው ከካህናቱ ልጆች አያሌዎች፥ የአሳፍም ልጅ የዘኩር ልጅ የሚካያ ልጅ የመታንያ ልጅ የሸማያ ልጅ የዮናታን ልጅ ዘካርያስ፥
36 ፤ ወንድሞቹም ሸማያ፥ ኤዝርኤል፥ ሚላላይ፥ ጊላላይ፥ መዓይ፥ ናትናኤል፥ ይሁዳ፥ አናኒ የእግዚአብሔርን ሰው የዳዊትን የዜማውን ዕቃ ይዘው ሄዱ፤ ጸሐፊውም ዕዝራ በፊታቸው ነበረ።
37 ፤ በምንጭም በር አቅንተው ሄዱ፤ በዳዊትም ከተማ ደረጃ፥ በቅጥሩም መውጫ፥ ከዳዊትም ቤት በላይ እስከ ውኃው በር ድረስ በምሥራቅ በኩል ሄዱ።
38 ፤ ሁለተኛውም የአመስጋኞቹ ተርታ ወደ ግራ ሄደ፤ እኔና የሕዝቡም እኵሌታ በስተኋላቸው ነበርን፤ በቅጥሩም ላይ፥ በእቶኑ ግንብ በላይ እስከ ሰፊው ቅጥር ድረስ፥ ከኤፍሬምም በር በላይ፥
39 ፤ በአሮጌው በርና በዓሣ በር በሐናንኤልም ግንብ፥ በሃሜአ ግንብ እስከ በጎች በር ድረስ ሄዱ፤ በዘበኞችም በር አጠገብ ቆሙ።
40 ፤ እንዲሁ ሁለቱ የአመስጋኞች ተርታዎች በእግዚአብሔር ቤት ቆሙ፤ ከእነርሱም ጋር እኔና የአለቆች እኵሌታ፥
41 ፤ ካህናቱም ኤልያቄም፥ መዕሤያ፥ ሚንያሚን፥ ሚካያ፥ ኤልዮዔናይ፥
42 ፤ ዘካርያስ፥ ሐናንያ መለከት ይዘው፥ መዕሤያ፥ ሸማያ፥ አልዓዛር፥ ኦዚ፥ ይሆሐናን፥ መልክያ፥ ኤላም፥ ኤጽር ቆምን። መዘምራኑም በታላቅ ድምፅ ዘመሩ፥ አለቃቸውም ይዝረሕያ ነበረ።
43 ፤ እግዚአብሔርም በታላቅ ደስታ ደስ አሰኝቶአቸዋልና በዚያ ቀን ትልቅ መሥዋዕት አቀረቡ፥ ደስም አላቸው፤ ሴቶቹና ልጆቹም ደግሞ ደስ አላቸው፤ የኢየሩሳሌምም ደስታ ከሩቅ ተሰማ።
44 ፤ ይሁዳም በአገልጋዮቹ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ስላላቸው፥ የካህናቱንና የሌዋውያኑን እድል ፈንታ እንደ ሕጉ ከከተሞች እርሻዎች ያከማቹ ዘንድ ለእጅ ማንሣት ቍርባንና ለበኵራት ለአሥራትም በየዕቃ ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎች ተሾሙ።
45 ፤ እነርሱም መዘምራኑና በረኞቹም የአምላካቸውን ሥርዓት የመንጻታቸውንም ሥርዓት እንደ ዳዊትና እንደ ልጁ እንደ ሰሎሞን ትእዛዝ ጠበቁ።
46 ፤ አስቀድሞም በዳዊትና በአሳፍ ዘመን እግዚአብሔርን በዜማ ለማመስገንና ለማክበር የመዘምራን አለቆች ነበሩ።
47 ፤ እስራኤልም ሁሉ በዘሩባቤልና በነህምያ ዘመን ለመዘምራኑና ለበረኞቹ እድል ፈንታቸውን በየዕለቱ ይሰጡ ነበር፤ የተቀደሰውንም ነገር ለሌዋውያን ሰጡ፥ ሌዋውያኑም ከተቀደሰው ነገር ለአሮን ልጆች ሰጡ።