መጽሐፈ ነህምያ።

1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13


ምዕራፍ 7

እንዲህም ሆነ፤ ቅጥሩ ከተሠራ በኋላ፥ ሳንቃዎቹንም ካቆምሁ በኋላ፥ በረኞቹና መዘምራኑ ሌዋውያኑም ከተሾሙ በኋላ፥
2 ፤ ወንድሜን አናኒንና የግንቡን አለቃ ሐናንያን በኢየሩሳሌም ላይ ሾምኋቸው፤ እርሱም እውነተኛ ከሌሎቹም ይልቅ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበረ።
3 ፤ እኔም። ፀሐይ እስኪሞቅ ድረስ የኢየሩሳሌም በሮች አይከፈቱ፤ እነርሱም ቆመው ሳሉ ደጆቹን ይዝጉ፥ ይቈልፉም፤ ከኢየሩሳሌምም ሰዎች አንዳንዱን በየተራው አንዳንዱንም በየቤቱ አንጻር ጠባቆችን አስቀምጡ አልኋቸው።
4 ፤ ከተማይቱም ሰፊና ታላቅ ነበረች፤ በውስጥዋ የነበሩ ሕዝብ ግን ጥቂቶች ነበሩ፥ ቤቶቹም አልተሠሩም ነበር።
5 ፤ አምላኬም ታላቆቹንና ሹማምቱን ሕዝቡንም ሰብስቤ እቈጥራቸው ዘንድ በልቤ አደረገ፤ አስቀድመው የመጡትን ሰዎች የትውልድ መጽሐፋቸውን አገኘሁ፥ በእርሱም እንደዚህ ተጽፎ አገኘሁ።
6 ፤ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው።
7 ፤ ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከአዛርያስ፥ ከረዓምያ፥ ከነሐማኒ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከበላሳን፥ ከሚስጴሬት፥ ከበጉዋይ፥ ከነሑም፥ ከበዓና ጋር መጡ።
8 ፤ የእስራኤልም ሕዝብ ሰዎች ቍጥር ይህ ነው፤ የፋሮስ ልጆች፥ ሁለት ሺህ መቶ ሰባ ሁለት።
9 ፤ የሰፋጥያስ ልጆች ሦስት መቶ ሰባ ሁለት።
10 ፤ የኤራ ልጆች፥ ስድስት መቶ አምሳ ሁለት።
11 ፤ ከኢያሱና ከኢዮአብ ልጆች የሆኑ የፈሐት ሞዓብ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ አሥራ ስምንት።
12 ፤ የኤላም ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት።
13 ፤ የዛቱዕ ልጆች፥ ስምንት መቶ አርባ አምስት።
14 ፤ የዘካይ ልጆች፥ ሰባት መቶ ስድሳ።
15 ፤ የቢንዊ ልጆች፥ ስድስት መቶ አርባ ስምንት።
16 ፤ የቤባይ ልጆች፥ ስድስት መቶ ሀያ ስምንት።
17 ፤ የዓዝጋድ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ሀያ ሁለት።
18 ፤ የአዶኒቃም ልጆች፥ ስድስት መቶ ስድሳ ሰባት።
19 ፤ የበጉዋይ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ስድሳ ሰባት።
20 ፤ የዓዲን ልጆች፥ ስድስት መቶ አምሳ አምስት።
21 ፤ የሕዝቅያስ ወገን የአጤር ልጆች፥ ዘጠና ስምንት።
22 ፤ የሐሱም ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ ስምንት።
23 ፤ የቤሳይ ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ አራት።
24 ፤ የሐሪፍ ልጆች፥ መቶ አሥራ ሁለት።
25 ፤ የገባዖን ልጆች፥ ዘጠና አምስት።
26 ፤ የቤተ ልሔምና የነጦፋ ሰዎች፥ መቶ ሰማንያ ስምንት።
27 ፤ የዓናቶች ሰዎች፥ መቶ ሀያ ስምንት።
28 ፤ የቤትዓዝሞት ሰዎች፥ አርባ ሁለት።
29 ፤ የቂርያትይዓሪምና የከፊራ የብኤሮትም ሰዎች፥ ሰባት መቶ አርባ ሦስት።
30 ፤ የራማና የጌባ ሰዎች፥ ስድስት መቶ ሀያ አንድ።
31 ፤ የማክማስ ሰዎች፥ መቶ ሀያ ሁለት።
32 ፤ የቤቴልና የጋይ ሰዎች፥ መቶ ሀያ ሦስት።
33 ፤ የሁለተኛው ናባው ሰዎች፥ አምሳ ሁለት።
34 ፤ የሁለተኛው ኤላም ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት።
35 ፤ የካሪም ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ።
36 ፤ የኢያሪኮ ልጆች፥ ሦስት መቶ አርባ አምስት
37 ፤ የሎድና የሐዲድ የኦኖም ልጆች፥ ሰባት መቶ ሀያ አንድ።
38 ፤ የሴናዓ ልጆች፥ ሦስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ።
39 ፤ ካህናቱ፤ ከኢያሱ ወገን የዮዳኤ ልጆች፥ ዘጠኝ መቶ ሰባ ሦስት።
40 ፤ የኢሜር ልጆች፥ ሺህ አምሳ ሁለት።
41 ፤ የፋስኮር ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ አርባ ሰባት።
42 ፤ የካሪም ልጆች፥ ሺህ አሥራ ሰባት።
43 ፤ ሌዋውያኑ፤ ከሆዳይዋ ወገን የኢያሱና የቀድምኤል ልጆች፥ ሰባ አራት።
44 ፤ መዘምራኑ፤ የአሳፍ ልጆች፥ መቶ አርባ ስምንት።
45 ፤ በረኞቹ፤ የሰሎም ልጆች፥ የአጤር ልጆች፥ የጤልሞን ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የሐጢጣ ልጆች፥ የሶባይ ልጆች፥ መቶ ሠላሳ ስምንት።
46 ፤ ናታኒም፥ የሲሐ ልጆች፥ የሐሡፋ ልጆች፥
47 ፤ የጠብዖት ልጆች፥ የኬራስ ልጆች፥ የሲዓ ልጆች፥
48 ፤ የፋዶን ልጆች፥ የልባና ልጆች፥
49 ፤ የአጋባ ልጆች፥ የሰምላይ ልጆች፥ የሐናን ልጆች፥ የጌዴል ልጆች፥ የጋሐር ልጆች፥
50 ፤ የራያ ልጆች፥ የረአሶን ልጆች፥ የኔቆዳ ልጆች፥
51 ፤ የጋሴም ልጆች፥ የዖዛ ልጆች፥ የፋሴሐ ልጆች፥
52 ፤ የቤሳይ ልጆች፥ የምዑናውያን ልጆች፥
53 ፤ የንፉሰሲም ልጆች፥ የበቅቡቅ ልጆች፥ የሐቀፋ ልጆች፥ የሐርሑር ልጆች፥
54 ፤ የበስሎት ልጆች፥ የምሒዳ ልጆች፥ የሐርሻ ልጆች፥
55 ፤ የበርቆስ ልጆች፥ የሲሣራ ልጆች፥
56 ፤ የቴማ ልጆች፥ የንስያ ልጆች፥ የሐጢፋ ልጆች።
57 ፤ የሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች፤ የሶጣይ ልጆች፥ የሶፌሬት ልጆች፥ የፍሩዳ ልጆች፥
58 ፤ የየዕላ ልጆች፥ የደርቆን ልጆች፥ የጌዴል ልጆች፥
59 ፤ የሰፋጥያስ ልጆች፥ የሐጢል ልጆች፥ የፈከራት ልጆች፥ የሐፂቦይም ልጆች፥ የአሞን ልጆች።
60 ፤ ናታኒም ሁሉና የሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ።
61 ፤ ከቴልሜላ፥ ከቴላሬሳ፥ ከክሩብ፥ ከአዳን፥ ከኢሜር የወጡ እነዚህ ናቸው፤ ነገር ግን የአባቶቻቸውን ቤቶችና ዘራቸውን ወይም ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ያስታውቁ ዘንድ አልቻሉም፤
62 ፤ የዳላያ ልጆች፥ የጦብያ ልጆች፥ የኔቆዳ ልጆች፥ ስድስት መቶ አርባ ሁለት።
63 ፤ ከካህናቱም የኤብያ ልጆች፥ የአቆስ ልጆች፥ ከገለዓዳዊው ከቤርዜሊ ልጆች ሚስት ያገባ በስሙም የተጠራ የቤርዜሊ ልጆች።
64 ፤ እነዚህ በትውልድ መጽሐፍ ትውልዳቸውን ፈለጉ፥ ነገር ግን አልተገኘም፤ ከክህነትም ተከለከሉ።
65 ፤ ሐቴርሰታም። በኡሪምና በቱሚም የሚፈርድ ካህን እስኪነሣ ደረስ ከተቀደሰው ነገር አትበሉም አላቸው።
66
67 ፤ ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ከነበሩ ከሎሌዎቻቸውና ከገረዶቻቸው ሌላ ጉባኤው ሁሉ አርባ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ስድሳ ነበሩ፤ ሁለቱ መቶም አርባ አምስት ወንዶችና ሴቶች መዘምራን ነበሩአቸው።
68 ፤ ፈረሶቻቸውም ሰባት መቶ ሠላሳ ስድስት፥ በቅሎቻቸውም ሁለት መቶ አርባ አምስት፥
69 ፤ ግመሎቻቸውም አራት መቶ ሠላሳ አምስት፥ አህዮቻቸውም ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ሀያ ነበሩ።
70 ፤ ከአባቶች ቤቶች አለቆችም አያሌዎቹ ሰዎች ስለ ሥራው ስጦታ ሰጡ። ሐቴርሰታም አንድ ሺህ የወርቅ ዳሪክ፥ አምሳም ድስቶች፥ አምስት መቶ ሠላሳም የካህናት ልብስ በቤተ መዛግብት ውስጥ ሰጠ።
71 ፤ ከአባቶች ቤቶች አለቆችም አያሌዎቹ በሥራው ቤተ መዛግብት ውስጥ ሀያ ሺህ የወርቅ ዳሪክ፥ ሁለት ሺህ ሁለት መቶም ምናን ብር ሰጡ።
72 ፤ የቀሩትም ሕዝብ የሰጡት ሀያ ሺህ የወርቅ ዳሪክና ሁለት ሺህ ምናን ብር፥ ስድሳ ሰባትም የካህናት ልብስ ነበረ።
73 ፤ ካህናቱና ሌዋውያኑም፥ በረኞቹና መዘምራኑም ከሕዝቡም አያሌዎቹ፥ ናታኒምም፥ እስራኤልም ሁሉ በከተሞቻቸው ተቀመጡ።