መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ።

1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 14 15 16 17 18 19 20 21 22 23 24 25 26 27 28 29


ምዕራፍ 1

አዳም፥
2 ፤ ሴት፥ ሄኖስ፥ ቃይናን፥ መላልኤል፥
3 ፤ ያሬድ፥ ሄኖክ፥ ማቱሳላ፥ ላሜሕ፥
4 ፤ ኖኅ፥ ሴም፥ ካም፥ ያፌት።
5 ፤ የያፌት ልጆች፤ ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዴ፥
6 ፤ ያዋን፥ ቶቤል፥ ሞሳሕ፥ ቴራስ።
7 ፤ የጋሜርም ልጆች፤ አስከናዝ፥ ሪፋት፥ ቴርጋማ። የያዋንም ልጆች፤ ኤሊሳ፥ ተርሴስ፥ ኪቲም፥ ሮድኢ።
8 ፤ የካምም ልጆች፤ ኩሽ፥ ምጽራይም፥ ፉጥ፥ ከነዓን።
9 ፤ የኩሽም ልጆች፤ ሳባ፥ ኤውላጥ፥ ሰብታ፥ ራዕማ፥ ሰብቃታ። የራዕማም ልጆች፤ ሳባ፥ ድዳን።
10 ፤ ኩሽም ናምሩድን ወለደ፤ እርሱም በምድር ኃያል መሆንን ጀመረ።
11 ፤ ምጽራይምም ሉዲምን፥ ዐናሚምን፥ ላህቢምን፥
12 ፤ ነፍተሂምን፥ ፈትሩሲምን፥ ፍልስጥኤማውያን የወጡበትን ከስሉሂምን፥ ከፍቶሪምን ወለደ።
13 ፤ ከነዓንም የበኵር ልጁን ሲዶንን፥
14 ፤ ኬጢን፥ ኢያቡሳዊውን፥ አሞራዊውን፥
15 ፤ ጌርጌሳዊውን፥ ኤዊያዊውን፥ ዐርካዊውን፥
16 ፤ ሲኒያዊውን፥ አራዴዎንን፥ ሰማሪዎንን፥ አማቲን ወለደ።
17 ፤ የሴምም ልጆች፤ ኤላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድ፥ አራም፥ ዑፅ፥ ሁል፥ ጌቴር፥ ሞሳሕ።
18 ፤ አርፋክስድም ቃይንምን ወለደ፤ ቃይንምም ሳላን ወለደ፤ ሳላም ዔቦርን ወለደ።
19 ፤ ለዔቦርም ሁለት ልጆች ተወለዱለት፤ በዘመኑ ምድር ተከፍላለችና የአንደኛው ስም ፋሌቅ ተባለ፤ የወንድሙም ስም ዮቅጣን ነበረ።
20 ፤ ዮቅጣንም አልሞዳድን፥
21 ፤ ሣሌፍን፥ ሐስረሞትን፥ ያራሕን፥ ሀዶራምን፥
22 ፤ አውዛልን፥ ደቅላን፥ ዖባልን፥ አቢማኤልን፥
23 ፤ ሳባን፥ ኦፊርን፥ ኤውላጥን፥ ዮባብን ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ነበሩ።
24
25 ፤ ሴም፥ አርፋክስድ፥ ሳላ፥ ዔቦር፥ ፋሌቅ፥
26
27 ፤ ራግው፥ ሴሮሕ፥ ናኮር፥ ታራ፥ አብርሃም የተባለ አብራም።
28 ፤ የአብርሃምም ልጆች፤ ይስሐቅ፥ እስማኤል።
29 ፤ ትውልዳቸውም እንደዚህ ነው። የእስማኤል በኵር ልጅ ነባዮት፤ ከዚህ በኋላ ቄዳር፥ ነብዳኤል፥ መብሳም፥
30 ፤ ማስማዕ፥ ዱማ፥ ማሣ፥ ኩዳን፥ ቴማን፥
31 ፤ ኢጡር፥ ናፌስ፥ ቄድማ፤ እነዚህ የእስማኤል ልጆች ናቸው።
32 ፤ የአብርሃምም ገረድ የኬጡራ ልጆች፤ ዘምራን፥ ዮቅሳን፥ ሜዳን፥ ምድያም፥ የስቦቅ፥ ስዌሕ። የዮቅሳንም ልጆች፤ ሳባ፥ ድዳን።
33 ፤ የምድያምም ልጆች፤ ጌፌር፥ ዔፌር፥ ሄኖኅ፥ አቢዳዕ፥ ኤልዳዓ። እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ልጆች ነበሩ።
34 ፤ አብርሃምም ይስሐቅን ወለደ። የይስሐቅም ልጆች ዔሳውና እስራኤል ነበሩ።
35 ፤ የዔሳው ልጆች፤ ኤልፋዝ፥ ራጉኤል፥ የዑስ፥ የዕላም፥ ቆሬ።
36 ፤ የኤልፋዝ ልጆች፤ ቴማን፥ ኦማር፥ ስፎ፥ ጎቶም፥ ቄኔዝ፥ ቲምናዕ፥ አማሌቅ።
37 ፤ የራጉኤል ልጆች፤ ናሖት፥ ዛራ፥ ሣማ፥ ሚዛህ።
38 ፤ የሴይርም ልጆች፤ ሎጣን፥ ሦባል፥ ጽብዖን፥ ዓና፥ ዲሶን፥ ኤጽር፥ ዲሳን።
39 ፤ የሎጣንም ልጆች፤ ሖሪ፥ ሔማም፤ ቲሞናዕ የሎጣን እኅት ነበረች።
40 ፤ የሦባል ልጆች፤ ዓልዋን፥ ማኔሐት፥ ዔባል፥ ስፎ፥ አውናም። የጽብዖንም ልጆች፤ አያ፥ ዓና።
41 ፤ የዓና ልጅ፤ ዲሶን። የዲሶንም ልጆች፤ ሔምዳን፥ ኤስባን፥ ይትራን፥ ክራን።
42 ፤ የኤጽር ልጆች፤ ቢልሐን፥ ዛዕዋን፥ ዓቃን። የዲሳን ልጆች፤ ዑፅ፥ አራን።
43 ፤ በእስራኤልም ልጆች ላይ ገና ንጉሥ ሳይነግሥ በኤዶምያስ ምድር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው። የቢዖር ልጅ ባላቅ፤ የከተማይቱም ስም ዲንሃባ ነበረ።
44 ፤ ባላቅም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ የባሶራ ሰው የዛራ ልጅ ኢዮባብ ነገሠ።
45 ፤ ኢዮባብም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ የቴማን አገር ሰው ሑሳም ነገሠ።
46 ፤ ሑሳምም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ በሞዓብ ሜዳ ምድያምን የመታው የባዳድ ልጅ ሃዳድ ነገሠ፤ የከተማይቱም ስም ዓዊት ነበረ።
47 ፤ ሃዳድም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ የመሥሬቃ ሰው ሠምላ ነገሠ።
48 ፤ ሠምላም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ በወንዙ አጠገብ ያለችው የረሆቦት ሰው ሳኡል ነገሠ።
49 ፤ ሳኡልም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ የዓክቦር ልጅ በኣልሐናን ነገሠ።
50 ፤ በኣልሐናንም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ ሃዳድ ነገሠ፤ የከተማይቱም ስም ፋዑ ነበረ፤ ሚስቱም የሜዛሃብ ልጅ የመጥሬድ ልጅ መሄጣብኤል ነበረች፤ ሃዳድም ሞተ።
51 ፤ የኤዶምያስም አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ ቲምናዕ አለቃ፥ ዓልዋ አለቃ፥ የቴት አለቃ፥
52 ፤ አህሊባማ አለቃ፥ ኤላ አለቃ፥ ፊኖን አለቃ፥
53 ፤ ቄኔዝ አለቃ፥ ቴማን አለቃ፥ ሚብሳር አለቃ፥
54 ፤ መግዲኤል አለቃ፥ ዒራም አለቃ፤ እነዚህ የኤዶምያስ አለቆች ነበሩ።