መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ።

1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 14 15 16 17 18 19 20 21 22 23 24 25 26 27 28 29


ምዕራፍ 6

የሌዊ ልጆች፤ ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ።
2 ፤ የቀዓትም ልጆች፤ እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል።
3 ፤ የእንበረምም ልጆች፤ አሮን፥ ሙሴ፥ ማርያም። የአሮን ልጆች፤ ናዳብ፥ አብዮድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር።
4 ፤ አልዓዛር ፊንሐስን ወለደ፤ ፊንሐስ አቢሱን ወለደ፤
5 ፤ አቢሱም ቡቂን ወለደ፤ ቡቂም ኦዚን ወለደ፤
6 ፤ ኦዚም ዘራእያን ወለደ፤ ዘራእያም መራዮትን ወለደ፤
7 ፤ መራዮት አማርያን ወለደ፤
8 ፤ አማርያም አኪጦብን ወለደ፤ አኪጦብም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም አኪማአስን ወለደ፤
9 ፤ አኪማአስም ዓዛርያስን ወለደ፤
10 ፤ ዓዛርያስም ዮሐናንን ወለደ፤ ዮሐናንም ዓዛርያስን ወለደ፤ እርሱም ሰሎሞን በኢየሩሳሌም በሠራው ቤት ካህን ነበረ፤
11 ፤ ዓዛርያስም አማርያን ወለደ፤ አማርያም አኪጦብን ወለደ፤
12 ፤ አኪጦብም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም ሰሎምን ወለደ፤
13 ፤ ሰሎምም ኬልቅያስን ወለደ፤ ኬልቅያስም ዓዛርያስን ወለደ፤
14 ፤ ዓዛርያስም ሠራያን ወለደ፤ ሠራያም ኢዮሴዴቅን ወለደ፤
15 ፤ እግዚአብሔርም ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን በናቡከደነፆር እጅ ባስማረከ ጊዜ ኢዮሴዴቅ ተማርኮ ሄደ።
16 ፤ የሌዊ ልጆች፤ ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ።
17 ፤ የጌድሶንም ልጆች ስም ይህ ነው፤ ሎቤኒ ሰሜኢ።
18 ፤ የቀዓትም ልጆች፤ እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል ነበሩ።
19 ፤ የሜራሪ ልጆች፤ ሞሖሊም፥ ሙሲ። የሌዋውያን ወገኖች በየአባቶቻቸው ቤቶች እነዚህ ናቸው።
20 ፤ ከጌድሶን፤ ልጁ ሎቤኒ፥ ልጁ ኢኤት፥ ልጁ ዛማት፥
21 ፤ ልጁ ዮአክ፥ ልጁ አዶ፥ ልጁ ዛራ፥ ልጁ ያትራይ።
22 ፤ የቀዓት ልጆች፤ ልጁ አሚናዳብ፥
23 ፤ ልጁ ቆሬ፥ ልጁ አሴር፥ ልጁ ሕልቃና፥
24 ፤ ልጁ አቢሳፍ፥ ልጁ አሴር፥ ልጁ ኢኢት፥ ልጁ ኡሩኤል፥ ልጁ ዖዝያ፥ ልጁ ሳውል።
25 ፤ የሕልቃናም ልጆች፤ አማሢ፥ አኪሞት።
26 ፤ የሕልቃናም ልጆች፤ ልጁ ሱፊ፥
27 ፤ ልጁ ናሐት፥ ልጁ ኤልያብ፥ ልጁ ይሮሐም፥ ልጁ ሕልቃና።
28 ፤ የሳሙኤልም ልጆች፤ በኵሩ ኢዮኤል፥ ሁለተኛውም አብያ።
29 ፤ የሜራሪ ልጆች፤ ሞሖሊ፥ ልጁ ሎቤኒ፥ ልጁ ሰሜኢ፥
30 ፤ ልጁ ዖዛ፥ ልጁ ሳምዓ፥ ልጁ ሐግያ፥ ልጁ ዓሣያ።
31 ፤ ዳዊትም ታቦቱ ዐርፎ ከተቀመጠ በኋላ በእግዚአብሔር ቤት ያቆማቸው የመዘምራን አለቆች እነዚህ ናቸው።
32 ፤ ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤት በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ በመገናኛ ድንኳን ማደሪያ ፊት እያዜሙ ያገለግሉ ነበር፤ በየተራቸውም ያገለግሉ ነበር።
33 ፤ አገልጋዮቹና ልጆቹ እነዚህ ናቸው፤ ከቀዓት ልጆች ዘማሪው ኤማን ነበረ፤ እርሱም የኢዮኤል ልጅ፥
34 ፤ የሳሙኤል ልጅ፥ የሕልቃና ልጅ፥ የይሮሐም ልጅ፥ የኤሊኤል ልጅ፥ የቶዋ ልጅ፥
35 ፤ የሱፍ ልጅ፥ የሕልቃና ልጅ፥ የመሐት ልጅ፥
36 ፤ የአማሢ ልጅ፥ የሕልቃና ልጅ፥ የኢዮኤል ልጅ፥ የዓዛርያስ ልጅ፥ የሶፎንያስ ልጅ፥
37 ፤ የታሐት ልጅ፥ የአሴር ልጅ፥
38 ፤ የአብያሳፍ ልጅ፥ የቆሬ ልጅ፥ የይስዓር ልጅ፥ የቀዓት ልጅ፥ የሌዊ ልጅ፥ የእስራኤል ልጅ ነው።
39 ፤ በቀኙም የቆመ ወንድሙ አሳፍ ነበረ፤ አሳፍም የበራክያ ልጅ፥
40 ፤ የሳምዓ ልጅ፥ የሚካኤል ልጅ፥ የበዓሤያ ልጅ፥
41 ፤ የመልክያ ልጅ፥ የኤትኒ ልጅ፥ የዛራ ልጅ፥
42 ፤ የዓዳያ ልጅ፥ የኤታን ልጅ፥ የዛማት ልጅ፥
43 ፤ የሰሜኢ ልጅ፥ የኢኤት ልጅ፥ የጌድሶን ልጅ፥ የሌዊ ልጅ ነው።
44 ፤ በግራቸውም በኩል ወንድሞቻቸው የሜራሪ ልጆች ነበሩ፤ ኤታን የቂሳ ልጅ፥ የአብዲ ልጅ፥
45 ፤ የማሎክ ልጅ፥ የሐሸብያ ልጅ፥ የአሜስያስ ልጅ፥
46 ፤ የኬልቅያስ ልጅ፥ የአማሲ ልጅ፥
47 ፤ የባኒ ልጅ፥ የሴሜር ልጅ፥ የሞሖሊ ልጅ፥ የሙሲ ልጅ፥ የሜራሪ ልጅ፥ የሌዊ ልጅ።
48 ፤ ወንድሞቻቸውም ሌዋውያን ለእግዚአብሔር ቤት ማደሪያ አገልግሎት ሁሉ ተሰጡ።
49 ፤ አሮንና ልጆቹ ግን የእግዚአሔር ባሪያ ሙሴ እንዳዘዘው ሁሉ ለቅድስተ ቅዱሳን ሥራ ሁሉ ስለ እስራኤልም ያስተሰርይ ዘንድ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ ይሠዉ ነበር፥ በዕጣኑም መሠዊያ ላይ ያጥኑ ነበር።
50 ፤ የአሮንም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ልጁ አልዓዛር፥
51 ፤ ልጁ ፊንሐስ፥ ልጁ አቢሱ፥ ልጁ ቡቂ፥
52 ፤ ልጁ ኦዚ፥ ልጁ ዘራእያ፥ ልጁ መራዮት፥
53 ፤ ልጁ አማርያ፥ ልጁ አኪጦብ፥ ልጁ ሳዶቅ፥ ልጁ አኪማአስ።
54 ፤ ማደሪያዎቻቸውም በየሰፈራቸው በየዳርቻቸው እነዚህ ናቸው፤ ለአሮን ልጆች ለቀዓት ወገኖች አንደኛው ዕጣ ነበረ።
55 ፤ ለእነርሱ በይሁዳ አገር ያለችውን ኬብሮንን፥ በእርስዋም ዙሪያ የነበረውን መሰምርያ ሰጡ፤
56 ፤ የከተማይቱን እርሻ ግን መንደሮችዋንም ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ሰጡ።
57 ፤ ለአሮንም ልጆች የመማፀኛውን ከተሞች፥ ኬብሮንን፥ ልብናንና መሰምርያዋን፥ ደግሞ የቲርን፥
58 ፤ ኤሽትሞዓንና መሰምርያዋን፥ ሖሎንንና መሰምርያዋን፥ ዳቤርንና መሰምርያዋን፥
59 ፤ ዓሳንንና መሰምርያዋን፥ ቤትሳሚስንና መሰምርያዋን፤
60 ፤ ከብንያምም ነገድ ጌባንና መሰምርያዋን፥ ጋሌማትንና መሰምርያዋን፥ ዓናቶትንና መሰምርያዋን ሰጡ። ከተሞቻተው ሁሉ በየወገናቸው አሥራ ሦስት ነበሩ።
61 ፤ ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች ከነገዱ ወገን ከምናሴ ነገድ እኵሌታ አሥር ከተሞች በዕጣ ተሰጡ።
62 ፤ ለጌድሶንም ልጆች በየወገናቸው ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴርም ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳንም ካለው ከምናሴ ነገድ፥ አሥራ ሦስት ከተሞች ተሰጡ።
63 ፤ ለሜራሪ ልጆች በየወገናቸው ከሮቤል ነገድ፥ ከጋድም ነገድ፥ ከዛብሎንም ነገድ፥ አሥራ ሁለት ከተሞች በዕጣ ተሰጡ።
64 ፤ የእስራኤልም ልጆች ለሌዋውያን ከተሞችን ከመሰምርያዎቻቸው ጋር ሰጡ።
65 ፤ ከይሁዳም ልጆች ነገድ፥ ከስምዖንም ልጆች ነገድ፥ ከብንያምም ልጆች ነገድ፥ እነዚህን በስማቸው የተጠሩትን ከተሞች በዕጣ ሰጡ።
66 ፤ ከቀዓትም ልጆች ወገኖች ለአንዳንዶቹ ከኤፍሬም ነገድ ከተሞች ድርሻ ነበራቸው።
67 ፤ በተራራማው በኤፍሬም አገር ያሉትን የመማፀኛውን ከተሞች ሴኬምንና መሰምርያዋን፥ ደግሞም ጌዝርንና መሰምርያዋን፥ ዮቅምዓምንና መሰምርያዋን፥
68 ፤ ቤትሖሮንንና መሰምርያዋን፥
69 ፤ ኤሎንንና መሰምርያዋን፥ ጋትሪሞንንና መሰምርያዋን ሰጡአቸው።
70 ፤ ከምናሴም ነገድ እኵሌታ ዓኔርንና መሰምርያዋን፥ ቢልዓምንና መሰምርያዋን ከቀዓት ልጆች ወገን ለቀሩት ሰጡ።
71 ፤ ለጌድሶን ልጆች ከምናሴ ነገድ እኵሌታ ወገን በባሳን ያለችው ጎላንና መሰምርያዋ፥ አስታሮትና መሰምርያዋ፤
72 ፤ ከይሳኮርም ነገድ ቃዴስና መሰምርያዋ፥ ዳብራትና መሰምርያዋ፥
73 ፤ ራሞትና መሰምርያዋ፥ ዓኔምና መሰምርያዋ፤
74 ፤ ከአሴርም ነገድ መዓሳልና መሰምርያዋ፥ ዓብዶንና መሰምርያዋ፥
75 ፤ ሑቆቅና መሰምርያዋ፥ ረአብና መሰምርያዋ፤
76 ፤ ከንፍታሌምም ነገድ በገሊላ ያለችው ቃዴስና መሰምርያዋ፥ ሐሞንና መሰምርያዋ፥ ቂርያታይምና መሰምርያዋ ተሰጡ።
77 ፤ ከሌዋውያን ለቀሩት ለሜራሪ ልጆች ከዛብሎን ነገድ ሬሞንና መሰምርያዋ፥ ታቦርና መሰምርያዋ፤
78 ፤ ከሮቤልም ነገድ በኢያሪኮ አንጻር በዮርዳኖስ ማዶ በምሥራቅ በኩል በምድረ በዳ ያለችው ቦሶርና መሰምርያዋ፥
79 ፤ ያሳና መሰምርያዋ፥ ቅዴሞትና መሰምርያዋ፥ ሜፍዓትና መሰምርያዋ፤
80 ፤ ከጋድም ነገድ በገለዓድ ያለችው ሬማትና መሰምርያዋ፥ መሃናይምና መሰምርያዋ፥
81 ፤ ሐሴቦንና መሰምርያዋ፥ ኢያዜርና መሰምርያዋ ተሰጡ።