መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ።

1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 14 15 16 17 18 19 20 21 22 23 24 25 26 27 28 29


ምዕራፍ 25

ዳዊትና የሠራዊቱ አለቆችም ከአሳፍና ከኤማን ከኤዶታም ልጆች በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም ትንቢት የሚናገሩትን ሰዎች ለማገልገል ለዩ፤ በአገልግሎታቸውም ሥራ የሠሩ ሰዎች ቍጥር ይህ ነበረ።
2 ፤ ከአሳፍ ልጆች፤ ዘኩር፥ ዮሴፍ፥ ነታንያ፥ አሸርኤላ፤ እነዚህ የአሳፍ ልጆች በንጉሡ ትእዛዝ ትንቢት ከተናገረው ከአሳፍ እጅ በታች ነበሩ።
3 ፤ ከኤዶታም የኤዶታም ልጆች፤ ጎዶልያስ፥ ጽሪ፥ የሻያ፥ ሰሜኢ፥ ሐሸብያ፥ መቲትያ፥ እነዚህ ስድስቱ ለእግዚአብሔር ምስጋናና ክብር በመሰንቆ ትንቢት ከተናገረው ከአባታቸው ከኤዶታም እጅ በታች ነበሩ።
4 ፤ ከኤማን የኤማን ልጆች፤ ቡቅያ፥ መታንያ፥ ዓዛርዔል፥ ሱባኤ፥ ኢያሪሙት፥ ሐናንያ፥ ሐናኒ፥ ኤልያታ፥ ጊዶልቲ፥ ሮማንቲዔዘር፥ ዮሽብቃሻ፥ መሎቲ፥ ሆቲር፥ መሐዝዮት፤
5 ፤ እነዚህ ሁሉ ቀንደ መለከቱን ከፍ ያደርጉ ዘንድ በእግዚአብሔር ቃል የንጉሡ ባለ ራእይ የሆነው የኤማን ልጆች ነበሩ። እግዚአብሔርም ለኤማን አሥራ አራት ወንዶች ልጆችንና ሦስት ሴቶች ልጆችን ሰጠው።
6 ፤ እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት በጸናጽልና በበገና በመሰንቆም ይዘምሩ ዘንድ፥ በእግዚአብሔርም ቤት ያገለግሉ ዘንድ ከአባታቸው እጅ በታች ነበሩ፤ አሳፍም ኤዶታምም ኤማንም ከንጉሡ ትእዛዝ በታች ነበሩ።
7 ፤ የብልሃተኞቹም ቍጥር እግዚአብሔርን ለማመስገን ከሚያውቁ ከወንድሞቻቸው ጋር ሁለት መቶ ሰማንያ ስምንት ነበረ።
8 ፤ ሁሉም ተካክለው፥ ታናሹ እንደ ታላቁ፥ አስተማሪውም እንደ ተማሪው፥ ለሰሞናቸው ዕጣ ተጣጣሉ።
9 ፤ የፊተኛው ዕጣ ከአሳፍ ወገን ለነበረው ለዮሴፍ ወጣ፤ ሁለተኛው ለጎዶልያስ ወጣ፤ እርሱ ወንድሞቹም ልጆቹም አሥራ ሁለት ነበሩ፤
10 ፤ ሦስተኛው ለዘኩር ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
11 ፤ አራተኛው ለይጽሪ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
12 ፤ አምስተኛው ለነታንያ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
13 ፤ ስድስተኛው ለቡቅያ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
14 ፤ ሰባተኛው ለይሽርኤል ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
15 ፤ ስምንተኛው ለየሻያ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
16 ፤ ዘጠኝኛው ለመታንያ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
17 ፤ አሥረኛው ለሰሜኢ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
18 ፤ አሥራ አንደኛው ለዓዛርኤል ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
19 ፤ አሥራ ሁለተኛው ለሐሸብያ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
20 ፤ አሥራ ሦስተኛው ለሱባኤል ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
21 ፤ አሥራ አራተኛው ለመቲትያ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
22 ፤ አሥራ አምስተኛው ለኢያሪሙት ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
23 ፤ አሥራ ስድስተኛው ለሐናንያ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
24 ፤ አሥራ ሰባተኛው ለዮሽብቃሻ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
25 ፤ አሥራ ስምንተኛው ለሐናኒ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
26 ፤ አሥራ ዘጠኝኛው ለመሎቲ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
27 ፤ ሀያኛው ለኤልያታ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
28 ፤ ሀያ አንደኛው ለሆቲር ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
29 ፤ ሀያ ሁለተኛው ለጊዶልቲ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
30 ፤ ሀያ ሦስተኛው ለመሐዚዮት ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
31 ፤ ሀያ አራተኛው ለሮማንቲዔዘር ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ ወጣ።